Skip to main content
The Red Cross Emblem is a special protective sign
Login |  0 item(s): £ 0.00 Text size Sitemap Help
Advanced search
 

አማርኛ (Amharic)

This page contains Ge'ez script. Without proper rendering support, you may see question marks, boxes, or other symbols instead. You can download the PDF or read about multilingual support on wikipedia for help. 

የብሪታንያ ቀይ መስቀል (British Red Cross) ዓለም አቀፍ የማፈላለግ ሥራና የመልእክት አገልግሎት፣ በዓለም

ዙሪያ በጦር መሳሪያ ግጭት፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በስደት ምክንያት የተጠፋፉ

ቤተሰቦችን የማገናኘት ተግባር ያከናውናል፡፡ ከቤተሰብዎ ጋር ተለያይተው ከሆነ ልንረዳዎ እንችል ይሆናል፡፡ 

የብሪታንያ ቀይ መስቀል በሚከተሉት መንገዶች እርዳታ መስጠት ይችላል፡-

> የቤተሰብ አባላት ያሉበትን ማፈላለግ

ቤተሰቦች በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በስደት ምክንያት ሲለያዩ የጠፉትን የቤተሰብ አባላት በማፈላለግ እገዛ ማድረግ እንችላለን፡፡

> የቤተሰቡን ወሬ ማድረስ

በጦርነት ወይም በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የተለመዱት የመገናኛ አውታሮች ሲፈራርሱም የቀይ መስቀል መልእክቶች በጭንቀት ላይ

ላሉት ቤተሰቦች ሊደርሱ ይችላሉ፡፡

(እባክዎ ገንዘብ ወይም ዕቃ መላክ እንደማይቻል ልብ ይበሉ፡፡)

> የእስር ማረጋገጫ

በእስራት ላይ እያሉ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ተጎብኝተው ከነበረ መታሰርዎን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ልንሰጥዎ

እንችል ይሆናል፡፡

የምንሠጣቸው አገልግሎቶች በሙሉ ነጻና ምሥጢራቸው የተጠበቀ ነው፡፡

የብሪታንያ ቀይ መስቀል ሰብዓዊ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው ሌሎች ሁኔታዎችም ለምሳሌ ያህል ውጭ አገር ከሚኖር አረጋዊ ዘመድ ጋር

ያለው ግንኙነት ድንገት በሚቋረጥበትም ጊዜ እነዚህን አገልግሎቶች ይሰጣል፡፡ 

ልንረዳዎ እንደምንችል ከተሰማዎ ያነጋግሩን

አንድ የብሪታንያ ቀይ መስቀል ተወካይ ጥያቄዎን ተቀብሎ በደስታ ያስተናግድዎታል፡፡

እንግሊዝኛ መናገር የማይችሉ ከሆነ የሚረዳዎትን አንድ አዋቂ የቤተሰብ አባል፣ የሥራ ባልደረባ ወይም ጓደኛ ይዘው መምጣት ይችላሉ፡፡

ወይም አስተርጓሚ ልናዘጋጅልዎ እንሞክራለን፡፡

ብዙ ጥያቄዎችን ያካተተ ቅጽ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ፡፡ የቻሉትን ያህል መረጃ እንዲሰጡን እንፈልጋለን፡፡ ቅጹን በመሙላት እናግዝዎታለን፡፡

ይህንን መረጃ ዘመዶችዎ ይኖራሉ ብለው የሚያስቡበት አገር ውስጥ ወደሚገኘው ብሔራዊ ቀይ መስቀል ወይም ቀይ ጨረቃ ማኅበር

ወይም ወደ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) እንልከዋለን፡፡ እነርሱም ያፈላልጓቸዋል፡፡ ሰዎችን የማፈላለግ ችሎታችን በአካባቢው

ባሉት ሁኔታዎች እንዲሁም በዚያ አገር ባለው የፀጥታ ሁኔታ ላይ የተመካ ነው፡፡

አንድ መረጃ ስናገኝ ወዲያውኑ እንዲያውቁት እናደርጋለን፡፡ ሆኖም ጥያቄዎን ማስተናገድ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ በእርግጠኝነት

ልንነግርዎ አንችልም፡፡ 

Contact your nearest Red Cross Office

AccessibilityContactLegalPrivacy
© British Red Cross 2010
British Red Cross, UK Office, 44 Moorfields, London EC2Y 9AL Phone: 0844 871 11 11. Fax: 020 7562 2000.

The British Red Cross Society, incorporated by Royal Charter 1908, is a charity registered in England and Wales (220949) and Scotland (SC037738).