Get help as a refugee - Amharic

እንደ ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ እርዳታ ያግኙ

ስደተኛ፣ ጥገኝነት ጠያቂ ወይም ለጥቃት ተጋላጭ የሆነ ስደተኛ ከሆኑ የ British ቀይ መስቀል ሊረዳዎት ይችላል፡፡

እንዴት ልንረዳ እንደምንችል

ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ሌላ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞች ለሚኖራቸው አንገብጋቢ ፍላጎት እርዳታ እንሰጣለን፡፡ የምንሰጠው እርዳታ እርስዎ ባሉበት ቦታ ላይ ይመረኮዛል፡፡ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡-

  • እሽግ ምግቦች እና ኩፖኖች
  • አነስተኛ ገንዘብ
  • ልብሶች
  • የሽንት ቤት መገልገያዎች
  • ብርድልብስ
  • የህጻናት እቃዎች፡፡

ተጨማሪ እርዳታ ልንሰጥ እችላለን፡፡ ይህ ደግሞ ያሉበት ሁኔታ እና ቦታ ላይ ይመረኮዛል፡-

  • የጉዞ ኩፖን
  • ጥቅማ-ጥቅም እና የስራ የምክር አገልግሎት
  • የጤና እንክብካቤ - አጠቃላይ ሀኪም ወይም የጥርስ ሀኪም እንዲያይዎት ማስመዝገብ
  • ቀጠሮዎች ላይ ከእርስዎ ጋር መሄድ
  • ከ UK ህይወት ጋር ማላመድ
  • ማብራሪያ - ከአካባቢዎ ጋር እንዲተዋወቁ
  • ስሜታዊ ድጋፍ
  • የጠፉ ቤተሰቦችን ማገናኘት
  • ሌሎች ሰዎችን ማስተዋወቅ፡፡

በቅርበት የሚገኘውን የጥገኞች አገልግሎት ማግኘት

Find your local refugee service

እኛን ሲያነጋግሩ ከሰለጠኑ የጉዳይ ሰራተኞቻችን መካከል አንዱ እርዳታ ልንሰጥዎት እንደምንችል ለማወቅ ፍላጎትዎን ይገመግማል/ትገመግማለች፡፡ የማንችል ከሆነ፤ ወደሚችል አገልግሎት እንጠቁምዎታለን ወይም ለሚችል አገልግሎት ስምዎን እናወጣለን፡፡

እንግሊዝኛ የማይናገሩ ከሆነ አስተርጓሚ እናቀርባለን፡፡

የፖለቲካ ወይም የሀይማኖት አላማ የለንም፤ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች አናሳውቅዎትም፤ እርዳታችን ነጻ እና ሚስጥራዊ ነው፡፡

በአካባቢዎየሚገኘውንአገልግሎትእንዴት እንደሚጠቀሙ

እርዳታችንን የሚያገኙት ባሉበት ቦታ ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ የሚከተለውን በቅርብ የሚገኘውንየጥገኝነትአገልግሎትያነጋግሩ፡-

  • ያለቀጠሮ መሄድ (ያለቀጠሮ የሚኬድበት ማእከል ከሆነ)
  • ቀጠሮ መያዝ
  • ወደሌላድርጅትመመራትካለበት፡፡

ይህን አገልግሎት ከዚህ በፊት ተጠቅመውታል? እባክዎ አስተያየትዎትን [ይስጡን] when form is available

በህገ-ወጥ መንገድ ተዘዋውረው ከሆነ

በህገ-ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ ልንረዳዎት እንችላለን፡፡

እንደስደተኛ የሚያገኙትን እርዳታ በተመለከተ ድጋፍ እንዲሁም በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብዎት እና በህገ-ወጥ መንገድ የተዘዋወሩ ከሆኑ ተጨማሪ እርዳታ የት እንደሚያገኙ ምክር እንሰጣለን፡፡

ለወጣት ስደተኞች እርዳታ

ከ15 እስከ 25 አመት እድሜ የሆነ ስደተኛ ከሆኑ በአንዳንድ የ UK ቦታዎች እርዳታ ያገኛሉ፡፡

እንደወጣት ስደተኛ እርዳታ ያግኙ

ከጠፉ ቤተሰቦች ጋር መገናኘት (ከቤተሰብ ጋር ግንኙነትን ማስቀጠል)

ስደተኛ ከሆኑ በሚከተለው መንገድ ከቤተሰብዎጋርእንዲገናኙልንረዳዎትእንችላለን፡-

  • የቪዛ ማመልከቻ በማዘጋጀት መርዳት
  • ቤተሰብዎከእርስዎጋርእዲገናኝየበረራ ጉዞ ማዘጋጀት (ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት የመጓጓዣ እገዛ)

እርዳታ መስጠት የምንችለው በ UK አንዳንድ ቦታዎች ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት ቪዛ ለሚጠይቁ ብቻ ነው፤ የተጠባባቂ ዝርዝር ሊኖር ይችላል፡፡

የአካባቢ አገልግሎትን [local service] ያነጋግሩ (የስደተኛ አገልግሎት ዝርዝር አፋላጊ መገኛ) ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት እርዳታ እንደሚሰጡ ለማወቅ፡፡

የ British ቀይ መስቀል መመሪያ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት እርዳታን አስመልክቶ የ British ቀይ መስቀል መመሪያን ያንብቡ::